News Details Home / News Details

የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ምርቃት
National . 9th Jul, 2025

የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች ምርቃት

ኖላዊ ትምህርት ቤት ወደ አንደኛ ደረጃ ለመግባት የሚያስፈልጋቸውን የሦስት ዓመት የቅድመ መደበኛ ትምህርት በሚገባ ያጠናቀቁ 158 ህጻናትን አስመርቋል፡፡ በዕለቱም የኖላዊ የትምህርት አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መሥራች አባልና ሥራ አስኪያጅ እንጂነር ፀጋዬ ዮሴፍ ኖላዊ ትምህርት ቤት ከምንም በፊት የተማሪዎች ሥነ ምግባር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ ገልጸው ወላጆችም ልጆቻቸው ለላቀ ውጤት በቅተው ማየት እንዲችሉ ከትምህርት ቤቱ ጋር እጅና ጓንት ሆነው መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱኔ የተገኙ ሲሆን እሳቸውም የትምህርት ሥራ በጋራ በቅንጅት የሚሠራ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ በትብብር መንፈስ መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

0 Comments

Leave A Comment

Sing in to post your comment or singup if you don’t have any account.